“ዛሬ ህዝብ የምናወያየው ለጠቅላላ እውቀት ወይንም ተወያይተዋል ለመባል አይደለም፡ በተጨባጭ የእቅድ ግብዓት ለማድረግ ነው፡፡”
አቶ አደም ፋራህ
በአዲስ አበባ ደረጃ እየተካሄደ ያለው የህዝብ ውይይት መክፈቻ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመክፈቻቸው እንደተናገሩት
በቅርቡ ብልጽግና ፓርቲ ሀገር አቀፍ ጉባኤ አካሂዶ ልዩ ልዩ ሕዝብ የመጠቅሙ ውሳኔዎችን ማሳለፉ ይታወቃል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይህ ብቻ በቂ አይደለም ብሎ በማመን ሀገራችንን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚረዱ ሃሳቦችን እንደሚያጋራን በማሰብ ይሕንን ውይይት በሀገር አቀፍ ደረጃ አዘጋጅተናል ብለዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በውይይቱ ለይስሙላ የህዝቡን እሮሮ ለመስማት ሳይሆን በጥልቀት በየአካባቢው በሁሉም መስክ የሚነሱ ጥያቄዎችን በማሰባሰብ በሂደት ምላሽ መስጠትን ግብ ያደረገ ነው ብለዋል።
ከንቲባ አዳነች ጨምረው እንደተናገሩት አጠቃላይ በከተማችን በሁሉም ቁልፍ መስኮች በሂደት መተግበር ያለባቸው በርካታ ጠቃሚ ግብአቶች አሁን በምናከናውነው ሕዝባዊ ውይይት ይገኙበታል ብለን እናምናለን ለዚህም ሁሉም ተሰብሳቢ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራሕ በውይይቱ መግቢያ ላይ እንደተናገሩት የአዲስ አበባ ሕዝብ ከ1997አንስቶ በሀገራችን ዴሞክራሲ እንዲዳብር ሁሉን አቀፍ ትግል በማድረግ እንዲሁም በሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም በነቂስ ወጥቶ በመመረጥ የበኩሉን ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሕዝብ በድርቅና በጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ በማድረግ ፣የሀገር መከላከያ ሠራዊት የኋላ ደጀን መሆኑን በተግባር ለማረጋገጥ በተመሣሣይ በዘላቂነት በዘላቂነት ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በተጨማሪም ለልዩ ልዩ ዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች እንግዶች ሲመጡ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ በማድረግ የሀገራችንን ገጽታ በበጎ ጎኑ እየገነባ ያለ ሕዝብ ነውም ብለዋል አቶ አደም ፋራህ።
አዲስ አበባን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት መዳረሻ ከተማ ለማድረግ ብልጽግና ፓርቲ የለቀ ትኩረት ሰቶ እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አደም ፋራህ ለዚህም ተፈጻሚነት መላው የከተማው ነዋሪ ድጋፍ ማድረግ የሚኖርበት ሲሆን ፖለቲከኞች እና የማሕበረሰብ አንቂዎች ከከፋፋይ ሃሳቦች እራሳቸውን አርቀው ለከተማይቱ ሁለንተናዊ ዕድገት በአንድነት እንዲቆም ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
ከለውጡ ወዲህ ብልጽግና ፓርቲ አዲስ አበባ ከተማችን የብልፅግና ተምሳሌት የሀገራችንን የፖለቲካ ፣የኢኮኖሚ እንዳሁም የዲፕሎማሲ መዕከል እንድትሆንም እየተሰራ ነው ብለዋል ምክትል ፕሬዝዳንቱ ለዚህም በርካታ ተጨባጭ ስራዎችን አከናውኗል ያሉ ሲሆን አሁንም ነዋሪው ከፓርቲውና ከመንግስት ጎን ተቀራርቦ እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ቀጥሎም ከንቲባ አዳነች አቤቤ የብልፅግና ፓርቲ የጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ለተሰብሳቢው ያቀረቡ ሲሆን በቀጣም ውይይቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡