“ለልጆቻችን ሰላምን እንጅ ጦርነት እና ችግርን አናወርስም”!!
በየካ ክ/ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳይ ከአስተዳደሩ ጋር ተወያይተዋል።
የ(TPLF) አሸባሪ ቡድን ለትግራይ ህዝብ የወገነ መስሎ በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጫና እና በደል ሊቆም ይገባል ሲሉ ተወላጆቹ ድርጊቱን ኮንነዋል።
የትግራይ ህዝብና የህወሀት ቡድን የተለያዩ ናቸው የትግራይ ህዝብ ሰላም ወዳድ እና ከሌሎች ብሔር ብሔረሰብ ወድምና እህቶቹ ጋር ተስማምቶ የሚኖር ህዝብ በመሆኑ ዓላማ ለሌለው ጦርነት ህዝቡ እየተሰቃየ በመሆኑ መንግስት ሊደርስለት ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ከጦርነት የሚገኝ መፍተሄ የለም ሰላምን በመመረጥ ህዝብን ከችግር ማውጣት ይገባል ሲሉ ተወላጆቹ ተናግረዋል።
ለመጭው ትውልድ ለልጆቻችን ሰላም እንጅ ጦርነት አናወረወስም፤ ከመንግስት ጎን በመቆም የትግራይ ህዝብ ብሎም በሀገራችን ሰላም እንዲሰፍን አብሮነታችን እናሳያለን ብለዋል።