የከተማ አስተዳደሩ ለበዓል በተለየ መልኩ የገበያ ዋጋ መረጋጋት እንዲችል አስቀድሞ ከአምራቾች ጋር ትስስር በመፍጠር ምርቶች በስፋት እንዲገቡ ሲሰራ ቆይቷል።
በዚህም ለዘመን መለወጫ የቁም ከብቶች የእንስሳት ተዋፅኦዎች ፤የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች እንዲሁም የተለያዩ የእህል ሰብሎች በሽማች ማህበራትና በነጋዴዎች በብዛት ማቅረብ ተችሏል።
ይህንን የገለፁት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ ሲሆኑ በተለይ በዚህ የአዲስ አመት በዓል አላግባብ ዋጋ በመጨመር የዋጋ ንረት ለማስከተል የሚሞነጋዴዎች ለመቆጣጠር አስተዳደሩ ቀደም ሲል በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በርካታ ምርት በማስገባት ገበያው እጥረት እንዳይገጥምና ዋጋውም ሚዛናዊ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
በከተማዋ በሚገኙ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም በየአካባቢው የተቋቋሙ የእሁድ ገበያዎች ሰፊ የገበያ አማራጭ በመሆን ገበያውን ሚዛን መጠበቅ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
አሁንም ህብረተሰቡ ከእነዚህ አማራጪች በመሸመት ከህገወጥ ነጋዴዎች ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡