የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ለተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎችን በተመለከተ አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክል መመሪያ እንደተዘጋጀ የሚዘዋወረው መረጃ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡
ሕጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ታክሲዎች በተማሪዎች የሰርቪስ አገልግሎት ላይ በመሰማራታቸው በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየፈጠረ ይገኛልም ብለዋል፡፡
በቀጣይም የትራንስፖርት እጥረቱን በተመለከተ ግምገማ ተደርጎ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚቀመጥና ዝርዝር መረጃም የሚወጣ ይሆናል ተብሏል፡፡
በመሆኑም የተማሪዎች ሰርቪስን በተመለከተ አዲስ መመሪያ እስኪወጣ ከዚህ ቀደም አገልግሎቱን ሲሰጡ የነበሩ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ታክሲዎች በነበሩበት ሥራ እንዲቀጥሉ ጥሪ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል፡፡