የአዲስ አበባ ከተማ የጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ “በአዲሱ ምዕራፍ ጽዱ አዲስ አበባ” መርህ በከተማዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በየሳምንቱ ህብረተሰቡን ያሳተፈ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ በተቀናጀ መልኩ በዛሬው ዕለት ጀምሯል፡፡
በቦሌ፣ ልደታ ፣ቂርቆስ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ መርሀግብር የኤጀንሲው እና የክፍለ ከተሞች ከፍተኛ አመራሮች፣ የፅዳት አመባሳደሮች፣የጸጥታ አካላት ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ፣የጽዳት ሰራተኞች እና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል::
አዲስ አበባን ውብ ፣ጽዱ እና ለኑሮ የተመቸች ከተማ ፣ቱሪስት ተመራጭ እንድትሆን ለማድረግ በየሳምንቱ መጨረሻ ቀናት በተቋማት እና በሁሉም አካባቢዎች የጽዳት መርሀግብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኤጀንሲው አስታውቋል፡፡