የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ1.7 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባውን የታላቁ ቤተመንግስት የቅርስና የመኪና ማቆምያ ፕሮጀክት በ1.2 ሄክታር ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን አምፊ ቴአትር፣ባሕላዊ ምግብ ቤቶች፣ ሱቆችና ሌሎች መዝናቸዎች ከማካተቱም በላይ ከ1000 በላይ ተሸከርካሪዎችን፣ 40 የአካል ጉዳተኛ ተሸከርካሪዎችንና 12 የቱሪስት አውቶብሶችን ማቆም የሚያስችል እንደሆነ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ሕንጻው የመሬት ውስጥ ዋሻ ከአንድነት ፓርክ ጋር የተገናኘ በመሆኑ ፓርኩን ዓለም አቀፍ የቱሪስት መዳረሻ ክብር ያጎናጽፈዋል፡፡
ፕሮጀክቱን በዛሬው እለት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት የሚመረቅ ይሆናል፡፡