ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በመጠቀም አላስፋለጊ ዋጋ በመጨመር የጨው ዋጋ እንዲጨምር ባደረጉ ሶስት ቀጥታ አከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የንግድ ፈቃዳቸውን መሰረዝን ጨምሮ የንግድ ቤታቸው ታሽጎ ጉዳያቸውም በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን ገልጸዋል ።
ቢሮው መጭውን የዘመን መለወጫ በዓል ታሳቢ በማድረግ በሁሉም የሸማች ማህበራት ሱቆች አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች እየቀረበ መሆኑን የገለፁት ምክትል ኃላፊው የግብርና ና የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ቀጥታ ለማቅረብ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የሀሰት መረጃዎችን በሚያሰራጩ እና አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ የንግድ ተቋማት ላይ ህብረተሰቡ ጥቆማ በመስጠት የተለመደ ትብብር ማድረግ እንዳለበት አቶ መስፍን ጥሪ አቅርበዋል