“የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልን ይደግፉ ፤ወንድማማችነትን ያጠናክሩ ” በሚል መሪ ቃል በአሁን ሰአት በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
የገቢ ማሰባሰቢያዉ ከተመሰረተ የወራት ጊዜ ብቻ ያስቆጠረዉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከሌሎች ወንድም እና እህት ኢትዮጵያዉያን ጋር በመሆን ክልሉን ማጠናከር እና ማደራጀት አስፈላጊ በመሆኑ ክልሉን ለማገዝ ያለመ ፕሮግራም ነዉ፡፡
ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የግብርና ምርቶች፣ የቡና እና የቅመማቅመም እንዲሁም የማዕድናት ሀብት ያሉት ነው፤ በቱሪዝሙም ዘርፍ ግንባታዉ እየተከናወነ ያለዉ የኮይሻ ፕሮጀክትን ጨምሮ ትልልቅ ፓርኮች ያሉት ክልል ነው።
በመጀመሪያዉ ዙር የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብሩም የኢፌዴሪ ም/ ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።