ድጋፉን ያደረጉት በተለያዩ ክፍለ ከተምች የሚኖሩ አርሶአደሮች ፣ የአዲስአበባ የስፖርት ቤተሰብ ፤የትራንስፖርት ቢሮ፤ የሀይማኖት ተቋማት እና የተለያዩ ባለሀብቶች ናቸው ።
ድጋፉን የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የስራ ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊዉ አቶ ጃንጥራር አባይ ተረክበዋል ።
“እኔ እያለሁ ኢትዮጵያ አትፈርስም በሚል መሪ ቃል በተደረገው የድጋፍ ርክክብ ላይ ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩት አሸባሪዉ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በከፈተው ጦርነት ከፍተኛ የሆነ ወድመት ቢያስከትልም በ መላው ኢትዮጵያዊያን የጋራ ርብርብ ችግሩን ለመቅረፍ እየተደረገ ያለዉ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል ነዉ ያሉት።
ተገደን የገባንበት ጦርነት በድል እስኪጠናቀቅ ድረስም በሁለንተናዊ መልኩ የሚደረገው ድጋፍ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊትና የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከፍተኛ ምራልና አቅም የሚሆን በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን ያስተላለፉ ሲሆን እስከአሁንም ድረስ የየአቅሙን አስተዋጽኦ ላበረከተው መላው የከተማው ነዋሪዎች በተለይም ለአርሶአደሮች በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
ከተደረጉት ድጋፎች ዉስጥ 106 ሰንጋ፤ 157 በግና ፍየል 290 ኩንታል ማካሮኒ፤82 ኩንታል ዱቄት፤ 200 ኪ.ግ ቡና የተለያዩ አልባሳት ፤ የንፅህና መጠበቂያዎች ይገኙበታል ።
#አካባቢህን ጠብቅ!
#ወደ ግምባር ዝመት!
#መከላከያን ደግፍ!