የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ቡድን በሱፐር ሊግ አሸናፊ በመሆን ወደ የኢትዮጵያ ቤቲንግ ፕሪሚየር ሊግ በመሸጋገሩ ከፍተኛ ኩራት እና ደስታ ተሰምቶኛል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ቡድኑ ያስመዘገበው ውጤት የጥረት፣የአንድነት እና የታታሪነት ምልክት ነው ብለዋል።
በከፍተኛ ጥረት ፣በጠንካራ የቡድን ስራ እና ትብብር ይህን ውጤት ላስመዝገባችሁ የእግር ኳስ ቡድኑ አባላት በራሴ እና በከተማችን ነዋሪዎች ስም ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ከንቲባ ዋ ቡድኑ በቤቲንግ ፕሪሚየር ሊጉ አመርቂ ውጤት እንዲያስመዘግብ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
በባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ሱፐር ሊግ ተወዳድረው በየምድባቸው አንደኛ ደረጃን በመያዝ በዘንድሮው የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ላለፉት የቡድኑ አባላት ለእያንዳንዳቸው እስከ 200 ሺህ ብር በጠቅላላው የአምስት ሚሊየን ብር የማበረታቻ ሽልማት መሰጠቱን የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር በላይ ደጀን ገልጸዋል ።
ማምሻውን በተካሄደው የሽልማት እና እውቅና መርሐግብር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ ፣ከፍተኛ አመራሮች እና የኢትዮጵያ እግር ኳስፌዴሬሽን አመራሮች ተገኝተዋል ።