መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገው እና ለ22ኛ ጊዜ የተካሄደው የዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በሰላም ተጠናቋል፡፡
ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ.ም የተካሄደው ይህ የሩጫ ውድድር የፕሮግራሙ አዘጋጆች፣ አስተባባሪዎች እና የውድድሩ ተሳታፊዎች ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራታቸው በስኬት ማጠናቀቅ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቆ ለዚህም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ ሁሉ በፀጥታ አካላት ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡