“ሕጻናት የነገ ተስፋ ለአዲስ አበባ” በሚል መሪ ቃል ላስጀመርነው የቀዳማይ ልጅነት ንቅናቄ ትግበራ ልዩ ትኩረት ሰጥተን በ90 ቀናት ውስጥ የሚሰሩ ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ ከክፍለ ከተሞች፣ ወረዳዎች እና ከባለድርሻ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት አመራሮች ጋር ተወያይተናል።
ከተማችንን ሕፃናት ቦርቀው፣ በአካልና በአዕምሮ ጎልብተው የሚያድጉባት ምርጥ የአፍሪካ መዲና በማድረግ ጠንካራ ትውልድ መገንባታችንን እንቀጥላለን።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ