ምርቶቹም በተለያዩ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች ይገኛሉ፡፡ በዚህም መሰረት የእሁድ ገበያዎች ከእሁድ ቀን በተጨማሪም እስከ አዲስ አመት ድረስ የሚዘልቁ ስለሆነ፣ ህብረተሰቡ ያለ አግባብ ዋጋ ከሚጨምሩና የኢኮኖሚ አሻጥር ከሚፈጥሩ አካላት ራሱን በመጠበቅ በየአካባቢው በሚገኙ የእሁድ ገበያዎችና የሸማች ማህበራት ሱቆች እንዲገበያይ ጥሪ እናቀርባለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ