ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ጳጉሜ 3 ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት የሚከበረውን የመልካምነት ቀን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው መልካምነት በማንኛውም ሁኔታ፣ ቦታና ጊዜ ለሰው ልጆች ሕይወት የሚበጀውን ነገር ማድረግ መሆኑን ገልጸዋል ።
መልካምነት በዘመናት ውስጥ ለሰው ልጆች የተሻለውን ነገር መስጠት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “መልካምነት ቀናነትን፣ መስጠትንና የገዛ ሥጋን ነክሶ ማየትን በውስጡ ይዟል” በማለት ገልጸዋል ።
መልካሞች የበዙባት ሀገር ብልጽግና ሩቅ አይሆንባትም ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ