ከመስቀል በዓል ጋር ተያይዞ ደመራ የበራባቸውን ስፍራዎችን ጨምሮ የመገበያያ ቦታዎችን እና የእንስሳት እርድ ተረፈ ምርቶችን የማፅዳት መርሀግብር ተከናውኖ
ኗል::
በቀጣይ ቀናትም የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚሳተፍበት የአደባባይ በዓል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከከተማ እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ኮሚቴ ተዋቅሮ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነም የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ገልፅዋል።
በዓሉን ጽዱና ምቹ በሆነ አካባቢና በሰላማዊ ሁኔታ እንዲከበር ለማስቻል አስተባባሪው ኮሚቴ የዘርፉ አካላትን ጨምሮ የከተማውን ነዋሪ ህብረተሰብና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን ዝግጁ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ኤጀንሲው አክሎ ገልፅዋል።
ከዚህም ጎን ለጎን ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ህብረሰቡ በየቤቱና በአካባቢው ያመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመሰብሰብ : በአይነቱ በመያዝና ለፅዳት ማህበራት በማስረከብ እንዲሁም ህገወጥ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በመከላከሉ ረገድ የዜግነት ኃላፊነቱን በመወጣቱ ኤጀንሲው አመስግኗል::