የቤተክህነቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበዓሉ አከባበር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ መግለጫ ስጥተዋል::
ባለፈው ዓመት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ በጥቂት ሰዎች በዓሉ መከበሩን ያወሱት ምክትል ስራ አስኪያጁ ዘንድሮ ተገቢውን የጥንቃቄ ተግባራት በመከወን በድምቀት ለማክበር ታስቧል ብለዋል::
በታሰበለት ጊዜና ድንቅ የግንባታ ስራ በተጠናቀቀው መስቀል አደባባይ ላይ የሚከበረው በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል::
የመስቀል በዓሉ በድምቀት እንዲከበር በርካታ የቤተክርስቲያኗ ኮሚቴዎች እየተንቀሳቀሱ ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ የበዓሉ ስነ ስርዓቶች እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ይከወናሉ ብለዋል::
AMN