በኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረት ስራ ኤጀንሲ የግብይትና መሰረተ ልማት ዳይሬክተር ወ/ሮ ደብሪቱ ለአለም እንደገለጽት ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ፤ ከገበሬዎች አምራች ህብረት ስራ ማህበራት፤ከኢንዱስትሪ ግብአት አምራች ፋብሪካዎች እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመቀናጀት መጪውን የፋሲካና የኢድ አልፈጥር በዓላትን መነሻ በማድረግ የምርት አቅርቦት እንዳይፈጠር ከወዲሁ በከተማዋ በሚገኙ በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ሱቆች አማካኝነት እየቀረቡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ለበዓሉ 1.5 ሚሊዮን ሊትሪ ዘይት፤ 120 ሺህ ኩንታል ስኳርና 41 ሺህ ኩንታል የስንዴ ዱቄት በሸማች፤ እንቁላል እስከ 1.2 ሚሊዮን፤ሽንኩርት እስከ 50 ሺህ ኩንታል ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንደሚቀርቡ ገልጸዋል፡፡
ሌላው በ11ዱም ክፍለ ከተሞች በሁሉም ወረዳዎች በሚገኙ የሸማህ ህብርት ስራ አማካኝነት በኤግዚብሽን ባዛራ አማካኝነት ለበአሉ የሚያስፈልጉ ምርቶች እንደሚቀርቡም ወ/ሮ ደብሪቱ ተናግረዋል ፡፡
በተጨማሪ በመደበኛ ነጋዴዎች በኩል ለበዓሉ ከ30-40 ሺህ የቁም እንሰሳት ለማቅረብ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 2ሺህ 200 የቁም ከብቶች በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል እንደሚቀርቡም ተገልጿል፡፡
የስረጭትና የአቅርቦት ስራዎች በበቂ ሁኔታ ተሳልጠው እንዲሄዱም ከከተማ እስከ መንደር የሚደርስ ግብረ-ሀይል ተቋቁሞ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ጠንከር ያለ የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች እንደሚደረጉ በመድረኩ ዳይሬክተሯ ገልፀዋል።
በተጨማሪም በቂ የግብርና፤አትክልትና ፍራፍሬ በተለይም ደግሞ ከ2 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ሽንኩርት ለግብይት እንደሚቀርብ የተገለጸ ሲሆን የግብርና ምርት አቅራቢዎች እና የልኳንዳ ማህበራትም በበቂ ሁኔታ መዘጋጀታቸውን ከገለጻው ለማወቅ ተችሏል።