የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የምክር ቤቱ ጽ/ቤት የፕሬስና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው የጉባኤው አጀንዳዎችን አስመልክክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ ምክር ቤቱ የአስተዳደሩን የስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸምን ይገመገማል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ፍርድ ቤቶች የስድስት ወራት አፈጻጸም፣ የመሬት ይዞታ ማስለቀቅ እና ካሳ ጉዳዮች አቤቱታ ሰሚ ጉባኤን ለማቋቋም የወጣ ረቂቅ ደንብ ተወያይቶ ማጽደቅ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶችን ማጽደቅም የምክር ቤቱ አጀንዳዎች ናቸው።