የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጃንጥራር አባይ ኢንዱስትሪዎች የሀገራችን ሀብት መሆናቸውን አምነን ያሉ ችግሮችን በጋራ እየፈታን ያደገና የበለፀገን ኢንዱስትሪ እንገነባለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ኢንዱስትሪዎች ሰላም እንዲሆኑ የአሰሪና ሰራተኞች አደረጃት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል፡፡
ቢሮው በሁሉም ቦታ በኢንዱስትሪዎች ምቹ የስራ ሁኔታ እንዲረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ይሰራል ያሉት ደግሞ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዩሐንስ ምትኩ ናቸው፡፡
ምቹ የስራ ሁኔታ የሚረጋገጠው ባለድርሻ አካላት በጋራ መስራት በመሆኑ ለተፈጻሚነቱ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አቶ ዩሐንስ ጠቁመዋል፡፡
በዘርፉ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ዓላማ፣ የባለድርሻ አካላት ዝርዝርና የስራ ሁኔታ በቢሮው የኢንዱስትሪ ሰላም የሙያ ደህንነት ጤንነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካሳ ስዩም ባቀረቡት መነሻ ሰነድ ላይ አብራተዋል፡፡
የጋራ ስምምነቱ ዓላማ ምቹ የስራ አካባቢና የስራ ሁኔታ በመፍጠር የኢንዱስትሪ ሰላምን ማረጋገጥና ምርታማነትን ማሳደግ መሆኑን አቶ ካሳ ተናግረዋል፡፡