በከተማዋ መሬት ጦም እንዳያድርና የፍጆታ ምርትን ለከተማው ህዝብ በበቂ ሁነታ ለማቅረብ “ምግባችን ከደጃችን” በሚል ሃሳብ በመላው አዲስ አበባ ስራው መጀመሩ ይታወቃል።
የዚሁ አካል የሆነ ዝግጅት በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ አማካኝነት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በ56 ሄክታር መሬት ላይ የከተማ ግብርና ስራ ተጀምሯል።
በመርሃ ግብሩ ወደከተማ ግብርናው ለተቀላቀሉ አዳዲስ የስራ እድል ተጠቃሚዎችም የመስሪያ ቦታ እና ሼድ ርክክብ ተደርጓል።