“አዲስአበባን ማሸበር “የሽብርተኞቹ ህወሃትና ሸኔ ከንቱ ምኞት ነው ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሸባሪዉ ህወሓትና ሸኔ አዲስአበባን በተደጋጋሚ የሽብር እና የንፁሀን ዕልቂት ማዕከል ለማድረግ አመቱን ሙሉ በተለያዩ መንገዶች ሲመክሩ ፣ ሲሰሩ፣ ነገርግን ሲከስሩ ፤ ከነ ግብረአበሮቻቸው እጅ ከፍንጅ ሲያዙ ከርመዋል ብለዋል ።
ይህ አሁንም ድረስ ያለቀቃቸው የሽብር ተግባር እና የንፁሀንን ህይወት የመቅጠፍ ክፉ ምኞት ሳይሳካላቸዉ ከነሙሉ ትጥቃቸው ከያሉበት መለቀማቸዉ ቀጥሏል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።
ተግባራቸው በከተማችን ነዋሪዎች ፣ በፀጥታ ሀይላችን እና በየደረጃው ባለዉ አመራር ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያን በሚጠብቀዉ ፈጣሪያችን ጥበቃ ክፉ ምኞታቸው መክሸፉን አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።
መላው የከተማችን ነዋሪ አካባቢዉን አሁንም በንቃት እንዲጠብቅ አደራ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ይህ በጦር ሜዳ ከፍተኛ ሽንፈትና ኪሳራ የደረሰበት አሸባሪ ቡድን እስከወዲያኛው እስኪደመሰስ ከፀጥታ ሀይሉ፤ በየ ደረጃዉ ካለ አመራርና ህዝባችን ጋር አስፈላጊ መረጃዎችን እየተለዋወጥን የከተማችንን ዘላቂ ሰላም እንደምናስቀጥል ያለኝን ሙሉ እምነት እገልፃለሁ ብለዋል።
በዛሬው ዕለትም አሸባሪዎችን የማደን ኦፕሬሽን ላይ የተሳተፋችሁ የፀጥታ ሀይሎች ፤ መረጃ በመስጠት የሰላም ደጀንነታችሁን ያስመሰከራችሁ ነዋሪዎች በመላው የከተማችን ነዋሪ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ከልብ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል ።
አሸባሪዎች ይወድማሉ፤ ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ትቀጥላለች !!
አዲስአበባም እንደ ስሟ ታብባለች!!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!!