በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ምክትል ከንቲባው የስራ እድል ፈጠራ አሁንም የከተማ አስተዳደሩ ዋነኛው ትኩረት መሆኑን ተናግረው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑና መታወቂያ ያላቸው ወጣቶች እና ሴቶች ከብሎክ ደረጃ ጀምሮ ስራ ፈላጊ መሆናቸው ተረጋግጦና ተተችቶ የስራ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር መዘርጋቱንም ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩ የሚያስገነባቸው ሁሉም ፕሮጀክቶች ለስራ እድል ፈጠራ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ተደርጎ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የተናገሩት አቶ ጃንጥራር የተገነቡት ሼዶች ህግ እና አሰራሩን ጠብቀው የስራ እድል ለሚፈጠርላቸው ዜጎች እንደሚተላለፉ እና በዚህም ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን የማረጋገጥ ስራ እንደሚከናወን ተናግረዋል።
ዛሬ በከተማ ደረጃ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ 158 ሼዶች በመመረቅ ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል::