ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው ህወሃት በእብሪት በከፈተብን ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው በአፋር ክልል በመጠለያ ጣቢያ በተጠለሉ 240 ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት መፈፀሙን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታውሰዋል፡፡
አሸባሪው ሃይል በሰነዘረው የጭካኔ ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን የተሰማቸውን ሃዘን በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ ለሟች ቤተሰቦች፣ ለአፋር ህዝብ እና ለመላ ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡
አሸባሪው ህወሃት ባንዳ ቡድን ዳግም የዚህ አይነት ጥፋት የመፈጸም እድል እንዳያገኝ መላው ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ ተያይዘው ግብአተ መሬቱን ለመፈጸም የተጀመረውን ትግል አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡