የበዓል ማክበሪያ ስጦታውን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስረክበዋል፡፡
አገልጋይነት ክብር ነው ፤ የራስን ሀገር እና ህዝብ ማገልገል ደግሞ ከክብርም በላይ ክብር ነው ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ማገልገል ታማኝነት፣ ቅንነትና ዝቅ ማለትን ይጠይቃል፤ እንደ መንግስት ህዝብን ለማገልገል በገባነው ቃል መሰረት በታማኝነት ለማገልገል የሚጠበቅብንን ሁሉ እንወጣን ብለዋል፡፡
ለአገልጋዮች እውቅናና ድጋፍ መስጠት ለቀጣይ ስራዎቻቸው ብርታት እና የሞራል ይሰጣል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ በአዲሱ ዓመት በታማኝነት ህዝባችንን የምናገለግልበት ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ ሲሉ መልዕከታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
#ማገልገልክብርነው በሚል በተካሄደው የአገልጋይነት ቀን መርሃግብር ከተለያዩ የእምነት ተቋሟት የተውጣቱ የእምነት አባቶች ሀገር እና ማህበረሰብን ማገልገል በሰውም ፣በፈጣሪም ዘንድ ያለውን ክብር ለተሳታፊዎች መልዕከት አስተላልፈዋል፡፡
የአዲሱን ዓመት በዓል በማስመልከት በተደረገው ስጦታም ለፊደራል ፖሊስ ፣ለአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ ደንብ ማስከበር ፣ ለፅዳት ሰራተኞች ፣ ለእሳት አደጋ ሰራተኞች የሰንጋ በሬዎችን ጨምሮ የዘይት ፣ የዶሮ እና የእንቁላል በተወካዮቻቸው አማካኝነት ርክክብ ተደርጓል፡፡