ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፍ መድረክ ስለታላቁ ህዳሴ ግድብ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን አቋሞችን በመወከል በሚታወቀው መሃመድ ከማል አልአሩሲ ቤት በመገኘት የቅዱስ ረመዳን የፆም ወር የአፍጥር ፕሮግራም ላይ በመገኘት በጋራ አፍጥረዋል።
እንኳን ለቅዱሱ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ በማለት ለመሃመድ አልአሩሲና ለቤተሰቡ መልካም የፆም ወቅት እንዲሆንላቸው ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተመኝተዋል፡፡
በዓለም መድረክ ላይ ኢትዮጵያን ከፍ በማድረግ ለሚሰብከው መሀመድ አል አሩሲ ቤት ነው የምንገኘው
ያሉት ምክትል ከንቲባዋ መሃመድን የምናውቀው ስለ ኢትዮጵያ ሲሞግት ነበር እናም ለአንተ ልዩ ክብር እና አክብሮት አለን የመጣነውም በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን አደረሰህ ልንልህ ነው በማለት ገልፀዋል፡፡
ይህን የጾም ወቅትም እጅግ ሰላማዊ ፣ በመተጋገዝ እና በመረዳዳት የበዛበት ሆኖ ማሳለፍ ይገባል ያሉት ወ/ሮ አዳነች ሙስሊም ከሙስሊሙ ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የክርስቲያን ወንድም እህቶቹ ጋር በመሆን የተለመደ የመረዳዳት እና የአብሮነት እሴቱን በማጠናከር ሊሆን ይገባል ብለዋል ።