በቁልፍ ርክክብ መርሐ ግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የከተማዋ ሀብት በእኩልነት እና በፍትሃዊነት ለህዝቡ መድረስ ይገባዋል፤ለዚህም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።የተጀመረው የልማት እና የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን ሁሉም መተባበር እና መተጋገዝ እንደሚገባው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቅርበዋል ።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ነጻነት ዳባ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ የመንግስት ቤቶችን በማስለቀቅ 85 ያህሉን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች እና አካል ጉዳተኞች ማስተላለፍ መቻላቸውን ገልጸዋል ።
እንዲሁም ለረጅም አመታት ተደራጅተው የመስሪያ ቦታ ሼድ ለመውሰድ ሲጠባበቁ ከቆዩ የስራ ዕድል የተፈጠረላቸው ዜጎች በ181 ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ 770 ሴቶች እና ወጣቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ 166 የመስሪያ ቦታ በዕጣ አስተላልፈዋል ።