በቤቶቹ ርክክብ መርሐግብር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት አዲስ አበባ ሀብታሙም ድሀውም በጋራ የሚኖሩባት ከተማ ናት ብለዋል ።በከተማዋ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ ቤቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው እና ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎች በመለየት በግልጽ እና በፍትሀዊነት እየተሰጠ መሆኑን ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።ነዋሪዎች ህጋዊነት እንዲሰፍን እና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋ ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ይታያል ደጀኔ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በህገወጥ መንገድ ከተያዙ 201 ቤቶችን በሁሉም ወረዳዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ እና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች መሰጠቱን ተናግረዋል ።በቀጣይም በህገወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን በማስለቀቅ ለችግረኛና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች የሚሰጥ መሆኑን አቶ ይታያል ገልጸዋል ።