ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ጋር በመሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሱማሌ ተራ አካባቢ በሚገኘው አሙዲን የተስፋብርሐን የምገባ ማዕከል በመገኘት በቀን አንድ ጊዜ መመገብ ከማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በዓልን አክብረዋል።
በአዲስ አመትን በማዕከሉ የምገባ አገልግልት ተጠቃሚ ከሆኑ የህብረተሰብ ከፍሎች ጋር ተገኝተው በዓሉን በማክበሬ ደሰታ ተሰምቶኛል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ያሉትን ዜጎች መደገፍ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆን አለበት ብለዋል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ላደረገው ድጋፍ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቹ ስም አመስግነዋል።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በበኩላቸው ሚድሮክ አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በስድሰቱ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የተስፋ ብርሐን የምገባ ማዕከላት 6 ሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡
አሙዲ የተስፋ ብርሃን የምግባ ማዕከል ከግንቦት ወር ጀምሮ በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ 2ሺህ ያህል ወገኖችን የምገባ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለየ ሁኔታ ዛሬ ዕለት በሌሎች የተስፋብርሃን የምገባ ማዕከላት የማዕድ ማጋራት መርሐግብር በመካሄድ ላይ ነው።