ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የኮቪድ -19 ወረርሽኝን ከገባ ጀምሮ በሽታውን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ግንባር ቀደም ለሆኑ የጤና ባለሙያዎች ክብር እና ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ።የኮቪድ -19 ክትባትም በቅድሚያ ለጤና ባለሙያዎች እንደሚሰጥ የገለፁት ወ/ሮ አዳነች ህብረተሰቡም ክትባቱ መጥቷል ብሎ ሳንዘናጋ የመከላከያ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ በበኩላቸው በኮቫክስ አማካኝነት ወደ ኢትዮጵያ የገባው የኮቪድ-19 ክትባት በዛሬው ዕለት በከተማዋ በሁሉም ጤና ተቋማት ለሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች ፣ በእድሜና በተጓዳኝ በሽታ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሠብ ክፍሎች በቅድሚያ እንደሚሠጥ ገልጸዋል፡፡