ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ።
የሚሊዮኖች እናት፣የእናትነት ፣ የደግነት፣ የፍቅር፣ የቆርጥነት እና የጥንካሬ ምሳሌ”ኢትዮጲያዊቷ ማዘር ትሬዛ” እያልን በበጎ ምግባራቸው የምናከብራቸዉ፤ የምንሳሳላቸዉ፤ ረጅም ዕድሜና ጤና ስንመኝላቸዉ የኖርን ተምሳሌታችን ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) በማረፋቸዉ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ።
ከእኛ በአካል ቢለዩም የጀግንነት እና የመልካምነት ስራቸው ከመቃብር በላይ በመሆኑ ሁሌም ሲወደሱ ፣ ሲታወሱ፣ ሲመሰገኑ እና በልባችን ህያው ሆነው ይኖራሉ ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደገነት ያኑርልን ብለዋል ።
ለልጆቻቸው ፤ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉ ፤ለመላዉ የከተማችን ሕዝብ መፅናናትን እመኛለሁ ፤የጀመሩት መልካም ስራ ለአፍታም እንደማይቋረጥ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ለመግለጽ እወዳለሁ ሲሉ ገልጸዋል ።