“መልካምነት ለሃገሬለ ወገኔ “በሚል በመከበር ላይ የሚገኘው የመልካምነት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል ፡፡
ቀኑን በማስመልከትም ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በመገኘት በበጎፈቃደኞች አማካኝነት ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የታደሱ ቤቶችን አስረክበዋል፡፡
አዲሱን ዓመት ስንቀበል አዲስ የኢትዮጵያ የድል ነፀብራቅ ብለን ሰይመን ፤የኢትዮጵያዊነት መገለጫ በሆነው የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህል በውስጣችን ያለውን መልካምነት በተግባር በማዋል ሁላችንም በአቅማችን በዓልን ማሳለፍ መቻል አለብን ብለዋል፡፡
በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎፍቃድ አገልግሎት መርሐግብር ባለሀብቶችን፣በጎፍቃደኛ ወጣቶችን እና ልዩ ልዩ ተቋማትን በማስተባበር በርካታ የአቅመ ቤቶችን እድሳት መደረጉን የገለፁት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው እለትም 1ሺህ 845 ቤቶችን በፍጥነት በማደስ ርክክብ ተደርጓል ብለዋል።
ይህ ቤት የማደስና መሰረታዊ የቤት ቁሳቁሶችን የማሟላት በጎ ተግባር በአረጋዉያኑ፤ በአጠቃላይ እገዛ በተደረገላቸዉ ወገኖቻችን ላይ የሚፈጥረው “የወገን አለኝ” ስሜት ጥልቅ ነዉ ያሉት ወ/ሮ አዳነች አብራችሁን ለሰራችሁ ፣ ላገዛችሁን ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
በዕለቱም በክፍለ ከተማው ለሚገኙ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ለበዓል የሚሆን የሰንጋ በሬ ስጦታ የተበረከተ ሲሆን ሲሆን 6 ሺህ 500 ለሚሆኑ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችለአቅመ ደካሞችም የተለያዩ የምግብ ቁሳቁሶችን አበርክተዋል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አባወይ ዮሐንስ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በ10ሩም ወረዳዎች ላይ ለ300 አረጋውያን የቤት እድሳትና ለ22ሺ345 ነዋሪዎች ደግሞ የማዕድ ማጋራት በማድረግ ላይ በማድረግ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡