ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከካቢኔ አባላት ጋር በመሆን ከማዘጋጃ እስከ መስቀል አደባባይ እየተሰራ ባለው የመንገድ ዳር ማስዋብ ፕሮጀክት ችግኝ ተክለዋል።
ለከተማዋ ውበት እና ለእንቅስቃሴ አመቺ የሆኑ የመንገድ አካፋይና ዳርቻን የማስዋብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።
በተለይ ከማዘጋጃ ቤት-የአድዋ 00 ኪሎሜትር ጀምሮ እስከ መስቀል አደባባይ ድረስ እየተሰራ ያለው ፕሮጀክት ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ እየተሰራ ያለ ሲሆን ለእግረኛ ፣ለሳይክል እና ለሌሎች አገልግሎቶች ምቹ ለማድረግ ደግሞ በመንገዱ አካፋይና ዳርቻ ላይ የችግኝ መትከል መርሐግብር መካሄዱን ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል ።
አዲስ አበባን እንደሰሟ ውብ እና አበባ ከተማ ለማድረግ የተጀመረው ስራ በሁሉም የከተማዋ መንገዶችና በተለያዩ አካባቢዎች ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።