ጉብኝቱ አየር ሀይላችን እየተካሄደ ያለውን ሪፎርም እና ለውጥ ለማየት እና የከተማ አስተዳደር የሚችለውን ድጋፍ ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የአየር ሀይላችን ከዚህ ቀደም ትኩረት ያልተሰጠው እና ከአቅሙ በታች ይሰራ የነበረ ተቋም መሆኑን የገለጹት ምክትል ከንቲባዋ አሁን ላይ መሰረታዊ ሪፎርም ተደርጎለት በዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት በሚችል ደረጃ ላይ መሆኑን መመልከት ችለናል ብለዋል።
የአየር ሀይላችን የኢትዮጵያን ሉዐላዊነት በማስጠበቅ አኩሪ ገድል እየፈጸመ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል ።
የከተማ አስተዳደሩም ለአየር ሀይል አባላት ደጀንነቱን ለመግለጽ የሰንጋ በሬዎችን ድጋፍ አድርጓል ።
በኢትዮጵያ አየር ኃይል በተካሄደው የጉብኝት መርሐግብር የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና የካቢኔ አባላት ተሳትፈዋል ።