‹‹ምግባችን ከደጃችን›› በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የግብርና ምርቶች ማሳያ ዓውደ-ርዕይ በሳይንስ ሙዚየም ተከፍቷል፡፡
በመክፈቻ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአፌዲሪ ግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቲ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዘ በአነስተኛ ቦታ የተትረፈረፈ ምርት ማምረት እንደሚቻል በዓውደ- ርእዩ ማሳየት ተችሏል ብለዋል፡፡ በአነስተኛ ቦታ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ተኪ ምርቶችን በማምረት ለሀገር ኢኮኖሚ የላቀ አስተዋጾዖ ማበርከት የሚቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ጅምር ያሳየ መሆኑን ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ ለአረንጓዴ ሽፋን ማደግ የላቀ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ በመሆኑ የከተማዋ የአረንጓዴ ሽፋን ምጣኔ ከፍተኛ መሻሻል እያሳየ መሆኑን ገልጸው ከተማ አስተዳደሩ የከተማ ግብርና ስራ እንዲስፋፋ ባደረገው ጥረትም ለበርካቶች የስራ ዕድል መፍጠር ከማስቻሉ ባሻገር ምርቶች ለገበያ እንዲቀርቡ በመደረጉ የኑሩ ውድነቱን መቋቋም ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡ ዓውደ ርዕዩ ከዛሬ ጀምሮ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል::