“የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለን ስለ አገራችን ሰብአዊ መብት ሁኔታ በተለይም ባለፉት ቀናት በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ /በሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ/ ስለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ አነጋግርያለሁ: ድርጊቱን በጽኑ አወግዛለሁ:: በየትም ቦታ የዜጎች ሕይወት ውድነቱና ክብሩ መሸርሸር የለበትም: ሞትን ከተለማመድነው ከግድያ በኃላ ከማውገዝና የሃዘን መግለጫ ከማውጣት አዙሪት አናልፍም: ከዚያ በላይ መሄድ ይኖርብናል::”
ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ