አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስና ውብ እንናደርጋለን ብሎም የቱሪዝም መተላለፍያ ሳይሆን የቱሪዝም መዳረሻ እናደርጋለን ብለን ስንነሳ፤ ህዝባችን የሰጠንን አደራ ፤ለማሳካት 24/7 ያለዕረፍት በትጋት እና በቁርጠኝነት በመረባረብ ነው፡፡
በከተማችን አዲስ አበባ አዲስና ዘመናዊ ከተማን እንደ አዲስ የማነፅ ያህል እርስ በእርሳቸው የተሳሰሩና የተናበቡ የእውቀት የውበትና የታሪክ፤ የምርምርና የእውቀት ማእከል እውን የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን ገፅታ ከመቀየር ባሻገር፤ የስራ እድልና የገቢ ምንጭም ናቸው።
ፕሮጀክቶችን በታለመላቸው ጊዜና በጀት ፤ጀምሮ ማጠናቀቅ፤ በጊዜ ለአገልግሎት ከማብቃት ባለፈ ሃገራዊ ስጋት የሆነብንን የሌብነት በር በመዝጋት በኩል፤ የራሱ የሆነ ሚና፤ መጫወት የሚችሉ ናቸው።
ይህንና ሌሎችም ታላላቅ ፕሮጀክቶች ሀሳብ ከማመንጨት ጀምሮ ያልተቆጠበ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የመሪነት ተምሳሌት ለሆኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ!
እንዲሁም ይህ ፕሮጀክት ጥራቱንና ውበቱን ጠብቆ በታለመለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ሌት ተቀን የሰራችሁ ኮንትራክተሮች ተቋራጮችና አማካሪዎች እና ፕሮጀክቱን ያስተባበራችሁና የመራችሁ የታላላቅ ፕሮጀክቶች ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞችም እንዲሁም ግንባታው በተለያዩ እክሎች እንዳይቋረጥና እንዳይዘገይ ግብዓቶችን በማቅረብና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ የተወጣችሁ ተቋማት እና አመራሮችም በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናችንን እናቀርባለን!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ !”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ