“#ትችያለሽ -በፈተና የተሞረደ ማንነት ለለውጥ የተመቸ ስብዕናን ይገነባል “በሚል በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው የሴቶች ተሳትፎ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
በምክክር መድረኩ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ ፣የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢ/ር አይሻ መሀመድ ፣ሴት ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ ሴት አመራሮች ተገኝተዋል ።

በምክክር መድረኩ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት የሴቶች የማቀድ እና የመፈጸም አቅምን እያሳደጉ ለሀገር ልማት ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ ብለዋል።በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ እየተከናወነ ባሉ ግዙፍ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በመምራትም ይሁን በመፈጸም የሴቶች ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለዚህም በርካታ ሴቶች የመሪነት ሚናቸው እያደገ ለመምጣቱ አንዱ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል ።
በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሴቶችን ሚና እና አርአያነት የሚያሳዩ የመነሻ ጥናቶች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።