የአዲስ አበባ ከተማ አመሰራረት

አዲስ አበባ ተብላ የተሠየመችው እቴጌ ጣይቱ ኅዳር ፲፬ ቀን ፲፰፻፸፱ ዓ/ም ፍልውሃ ፊል-ፊል ወደሚልበት መስክ ወርደው ሳሉ ከዚህ በፊት አይተዋት የማያውቋት አንዲት ልዩ አበባ አይተው ስለማረከቻቸው ቦታውን ‹‹አዲስ አበባ!›› አሉ ይባላል። አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ስትሆን በተጨማሪ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም የብዙ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅርንጫፎችና ሌሎችም የዓለም የዲፕሎማቲክ ልዑካን መሰብሰቢያ ከተማ ናት። ራስ-ገዝ አስተዳደር ስላላት የከተማና የክልል ማዕረግ ይዛ ትገኛለች። አብዛኞቹን የሀገሩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች የሚኖሩባት ከተማ ናት። ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኘው ከተማ በግምት 2,757,729 ሕዝብ የሚኖርባት በመሆኗ የሀገሪቱ አንደኛ ትልቅ ከተማ ናት።

ከተማዋ እቴጌ ጣይቱ በመረጡት ቦታ ማለትም በፍል ውሐ አካባቢ ላይ በባላቸው በዳግማዊ ምኒልክ በ፲፰፻፸፰ ዓ.ም. ተቆረቆረች። የሕዝቧ ብዛት በያመቱ 8% (ስምንት በመቶ) እየጨመረ አሁን አራት ሚሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል።

ከእንጦጦ ጋራ ግርጌ ያለችው መዲና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መገኛ ሆናለች። ይህም በመስራቹ የቀድሞው ንጉሠ ነገሥት ስም ቀዳማዊ ኀይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ይባል ነበር።

ክፍለ ከተማ

ክፍለ ከተማስፋትህዝብ ብዛት
ብዛት
አዲስ ከተማ7.41271,64436,659.1
አቃቂ ቃሊቲ118.08195,2731,653.7
አራዳ9.91225,99923,000
ቦሌ122.08328,9002,694.1
ጉለሌ30.18284,8659,438.9
ቂርቆሰ14.62235,44116,104
ኮልፌ ቀራኒዮ61.25546,2197,448.5
ልደታ9.18214,76923,000
ን/ስልክ ላፍቶ68.30335,7404,915.7
የካ85.46337,5753950.1
ለሚ ኩራN/AN/AN/A
ስምክፍለ ከተማየስራ መደብ
አቶ ይታያል ደጀኔአዲስ ከተማዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ አሰፋ ቶላአዲስ ከተማፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
ወ/ህይወት ጉግሳአዲስ ከተማም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ጀማል ረዲቂርቆስዋና ሥ/አስፈፃሚ
አሰግደው ኃ/ጊዮርጊስቂርቆስፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ታመነ አዱኛቂርቆስም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ መኮንን አምባዬቦሌዋና ሥ/አስፈፃሚ
ወ/ትዕግስት ደጀኔቦሌፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ በረከት ተሰማቦሌም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ አባዌ ዮሐንስጉለሌዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ሲሳይ እንዳለጉለሌፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ አሸናፊ ደጀኔጉለሌም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ አሸናፊ ደጀኔጉለሌም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
ወ/ሮ ፈቲያ መሐመድአቃቂዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ሙሰማ ጀማልአቃቂፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ግርማቸው አባተአቃቂም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
ወ/ነፃነት ዳባንፋስ ስልክ ላፍቶዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ዘመን ደሳለኝንፋስ ስልክ ላፍቶፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ተገኝ ድንቅነህንፋስ ስልክ ላፍቶም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ኤልያስ መሐመድለሚ ኩራዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ወንዳየሁ ደጀኔለሚ ኩራፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ብርሃኑ ስለአምላክለሚ ኩራም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
ወ/ሽታዬ መሐመድልደታዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ አንዳርጌ ተዋበልደታፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ታረቀኝ ገመቹልደታም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ሙቀት ታረቀኝኮልፌ ቀራንዮዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ በርሃኑ አበራኮልፌ ቀራንዮፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ሙሉቀን ዮሐንስኮልፌ ቀራንዮም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ አስፋው ተክሌየካዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ፈይሣ ፈለቀየካፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ አበራ አፍራሻየካም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ
ዶ/ር ሃናአራዳዋና ሥ/አስፈፃሚ
አቶ ሚደቅሳ ከበደአራዳፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
አቶ ሙባሪክ ከማልአራዳም/ዋና ሥ/አስፈፃሚ