ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ
አሁን ያሉ የመከላከያ አመራሮች ሲሾሙ ኢትዮጵያ ወግያ ውስጥ ነበረች፡፡ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ነው chief of staff, deputy chief of staff የሾምነው፡፡
አንድ አመት ኢትዮጵያን ከማፍረስ መታደግ ብቻ ሳይሆን ባባፉት 30 ዓመታት ከነበረን የሃገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥር አንፃር ምንም ሳይጋነን ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ሃይል ገንብተዋል፡፡
ባለፉት 30 ዓመታት ከነበረን የአየር ሃይል ምንም ሳላጋንን አስር ሃያ ሰላሳ እጥፍ የሚልቅ አየር ሃይል ገንብተዋል፡፡
ኢትዮጵያን ከማፍረስ የታደጉት ወታደሮቹን ፈንጂ እርገጥ ብለው እያዋጉ ነው፡፡
ስናዋጋቸው አንተ ኦሮሞ ነህ አንተ አማራ ነህ አላልናቸውም፡፡ኢትዮጵያዊ ነህ ብለን ነው ሙቱ ያልናቸው፡፡ አሸንፈው ሲመለሱ ግን እንትና ኦሮሞ ነው እንትና አማራ ነው የሚሉ ሰዎች ስሰማ ግን በጣም ልቤ ያዝናል፡፡
ለሃገር መከላከያ ሰራዊት በዚህ አጋጣሚ የማስተላልፈው መልእክት እናንተ ዘራችሁ ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዲያስፖራ የእራት ፕሮግራም ላይ ከተናገሩት የተወሰደ