በዚህ ወቅት ሁሉም የፖለቲካ ተንታኝ ነኝ በሚልበትና ምክንያታዊ ያልሆነ የፖለቲካ ትንታኔና ድምዳሜ ላይ የሚደረስበት በመሆኑ ማህበረሰቡ በዚያ እንዳይወሰድ ብርቱ ጥንቃቄ የሚጠይቅ ወቅት ነው።
በሃገራችን ባለፉት ዘመናት ለውጦች በሚገባ ባለመመራታቸው ምክንያት ተደናቅፈዋል። ለዚህም ነው ስትራቴጂክ በሆነ አመራርና ፅናት ባይመራ ኖሮ ይህ ለውጥ እንደሌሎቹ በመክሸፍ ራሱን ይደግም ነበር ፡፡
ስለሆነም ይህ ለውጥ ተቋማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ስክነት ያስፈልጋል ፤ ለውጡ ሂደቱን ጠብቆ እንዲሄድ በተቋም መምራትና ፅናት ወሳኝ ነው፡፡”
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ