በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ የሀይማኖት አባቶች፣የአገር ሽማግሌዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ጋር ዉይይት አካሂዷል ።
ኢትዮጵያን ከትዉልድ ትዉልድ በተላለፉ ልዩነቶች ምክንያት የተፈጠሩ መቃቃሮችን ማስወገድ ፤ ከዘመናት የግጭት አዙሪት ዉስጥ በመውጣት ዘላቂ ሰላም ማረጋጋጥ ይገባናል ብለዋል የዉይይቱ ተሳታፊዎች፡፡
እንደ አገር ገለልተኛ ተቋም በማቋቋም እና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ ብሔራዊ ዉይይት ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የሚበረታቱ እንደሆነም ገልጸዋል ፡፡
ተወያዮቹ እንደገለጹት እንደ ከተማ ብሎም እንደ አገር ቀጣይ ግባችን ተገደን የገባንበትን ጦርነት በድል በመደምደም ሙሉ ትኩረታችንን በሁለንተናዊ የአገር ልማትና እድገት ላይ ሊሆን ይገባል ብለዋል ።
በቀጣይም በወራሪው ቡድን ምክንያት ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ከማቋቋም ጎን ለጎን የወደሙ የተለያዩ የትምህርት እና የጤና ተቋማትን ለመገንባት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ቃል ገብተዋል ።
የዉይይት መድረኩን የመሩት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሳንፈልግ ተገደን የገባንበትን ጦርነት በተባበረ ክንድ በድል በማጠናቀቅ ፤ በጦርነቱ ተጎጂ የሆኑ አካለትን መልሶ የማቋቋም ስራ ማከናዋንና የታየዉን ከፍተኛ ህብረ ብሔራዊ አንድነትና መነሳሳት አሟጦ በመጠቀም በሁለንተናዊ የአገር ልማትና እድገት ላይ ትኩረት በማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡