በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር በመኪና ጥበቃ ላይ በተሰማሩ ነዋሪዎች ጥቆማ ከ2300 ካርቶን በላይ ዘይት ጭኖ የነበረ መኪና በኑሮ ውድነትና ገበያ ማረጋጋት ግብረ ሃይል ተወርሶ በወረዳው መሰረታዊ ሸማች ማህበር አማካኝነት ለህብረተሰቡ ሊከፋፈል መወሰኑን ወረዳው አስታወቀ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዝታ ነጋሽ የወረዳው አስተዳደር ኑሮ ውድነቱንና ገበያውን ለማረጋጋት ከዚህ ቀደምም በርካታ ስራዎችን ማከናወናቸውን አውስተው ህብረተሰቡ መሰል ህገወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በግብረ ሃይሉ ውሳኔ መሰረት በወረዳ 4 ነዋሪዎች ሸማች ሃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ለወረዳው ነዋሪዎች እንዲከፋፈል መወሰኑን የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዝታ አስታውቀዋል።