“እኛ የትግራይ ክልል ተወላጆች ለቀጣይ የኢትዮጵያ ሠላም የድርሻችንን እንወጣለን”በሚል መሪ ቃል የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታና ተዛማች ጉዳዮችን አስመልክቱ በክፍለ ከተማው ካሉ የትግራይ ክልል ተወላጆች ጋር ውይይት አካሄዷል።
በውይይቱ መንግስት ችግሮቹ ወደ ጦርነት ከማምራታቸው በፊት የተለያዩ የሠላም አማራጮችን ለሽብር ቡድኑ አቅርቦ ቢሆንም እኔ ያልመራዋት ሀገር ትፍረስ በሚል እሳቤ በህዝብ ላይ እልቂት በማወጅ የህዝብ ጠላት መሆኑን ሲያሳይ መቆየቱ የሚታወቅ ነው ስለዚህም የትግራይ ተወላጅ በወቅታዊ ሀገራዊ ውይይት ላይ ተሳታፋፊ በመሆን በሀገር ሠላም ዙሪያ የጋራ አቋም መያዝ ከመንግስት ጎን መቆም እንደሚያስፈልግም ተገልጿል።
በውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ የክልሉ ተወላጆች በመድረኩ የህዝባዊ ውይይቶች መደረጉን ወቅታዊና ተገቢ መሆኑን ጠቁመው የትግራይ ተወላጆች ለውጡ ሲመጣ ለውጡን የደገፈ ህዝብ ነው ሲሉ ነገር ግን ከትግራይ ተወላጆች ጋር የሚዘጋጁ ውይይቶችተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሠብለ አክለውም አሁናዊው የሀገራችን ሁኔታ የትግራይ ህዝብንና አሸባሪ ቡድኑን በአንድ ጨፍልቆ አንድናቸው የሚሉ እሳቤዎችን በማስወገድ ህዝብን ከሽብር ቡድኑ ነጥሎ ማየት ያስፈልጋል ሲሉ ህዝብን እየገደለ እና እያስገደል እናቶች የወላድ መካን እያደረግ ለህዝብ ቆሜአለው የሚል አመለካከት ያለው ይህ ቡድን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሊኖረው አይገባም ሲሉ ጨምረውም የክልሉ ተወላጆች ከሌሎች የክልል ተወላጆች ጋር በአንድነት፣በመከባበር፣በመግባባት እንዲሁም ያለምንም ልዩነት መብቶቹ ተጠብቀውለት መኖር አለበት ሲሉ ተደምጠዋል።