በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጽሚ ወ/ሮ መላኬ አለማየሁ የዳቦ ፋብሪካዎቹ አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት ያላቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አንስተዋል።
በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ የተባሉት የዳቦ ፋብሪካዎች ግንባታ በተፋጠነ ሁኔታ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው ወደ ማምረት እንደሚገቡ ወ/ሮ መላኬ ተናግረዋል።
በተለያዩ ወረዳዎች የሚገነቡት እነዚህ የዳቦ ፋብሪካዎች ግንባታ ወጪያቸው ሙሉ በሙሉ በክፍለ ከተማው በሚገኙ ባለሀብቶች እንደሚሸፈንም ገልጸዋል።