አዲስ አበባችን ለኑሮ ምቹ እናደርጋለን ስንል ለደሃውም ጭምር ምቹ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው።ዛሬም በልደታ ክፍለከተማ በህገወጦች ተይዘው የነበሩ 138 ቤቶችን ለአረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ የማስተላለፍያ ፕሮግራም ተካሂድዋል።ክፍለከተማው በዘንድሮ የበጀት አመት ያስተላለፋቸው ቤቶች ቁጥር በድምሩ 254 በማድረስ 1300 የሚሆኑ የክፍለከተማው ነዋሪዎችን ተጠቃሚ አድርጓል። ዛሬ ቤት ለተላለፈላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ከፊታችን ባለው ጊዜም ተጨማሪ ቤቶችን ለደሃ እንሰራለን እንጂ ፣ ደሃን አፈናቅሎ ለሀብታም መሸጥ እንዳይኖር እንሰራለን።