በአካል ብቃት እንቅስቃሴው ከፍተኛ የከተማ አመራሮች ፣የክ/ከተማና የወረዳ አመራሮች፣የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ተካሂዷል ።
በፕሮግራሙ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ እንደገለጹት ስፖርት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ አብሮነትን ፍቅርን የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀው የጤና ፖሊሲን መሰረት በማድረግ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል ስፖርት መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል ።
የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ከተማችንና ክ/ከተማችን አውነትም የሰላምና የአብሮነት ከተማ መሆናቸውን የታየበት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መሆኑን ጠቅሰው ፕሮግራሙን ያስተባበሩ እንዲሁም የተሳተፉ በየደረጃው የሚገኙ አካላትን አመስግነዋል ።