በመላው አለም ያስተጋባዉ የአፍሪካ ቀንድ ልጆች ድምፅ በታሪካችን ከፍታ ላይ በደማቅ ብዕር በድል አድራጊነት ከሚፃፉ ንቅናቄዎች አንዱ ነው ሲሉ የአዲሰ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማምሻውን ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት ፣ ኢትዮጵያውያንና የአፍሪካ ቀንድ ዳያስፖራዎች ያካሄዱት #nomore ንቅናቄ በየትኛውም ሀገር ዳያስፖራ ታሪክ መቼም ታይቶ የሚያውቅ አይደለም ብለዋል።
በታሪካችን ከፍታ ላይ በደማቅ ብዕር በድል አድራጊነት ከሚፃፉ ንቅናቄዎች አንዱ እንደሚሆን እምነቴ ነው ያሉት ይህንን ታላቅ ነጎድጓዳማ ድምፅ አለመስማትም ሆነ አለማክበር በፍጹም አይቻልም ብለዋል።
አካባቢህን ጠብቅ
ወደ ግንባር ዝመት
ሠራዊቱን ደግፍ