አዲስ መደበኛ መታወቂያ ለሰራተኞቻቸው የሚሰጡ አንዳንድ የመንግስትና የግል ተቋማት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ይገባል ተብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታው ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ቀንአ ያደታ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም አንዳንድ የግልና የመንግስት ተቋማት ለሰራተኞች መደበኛ መታወቂያ እየሰጡ ነው ብለዋል።
ይህ ደግሞ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ የማይፈቀድ መሆኑን ነው ሀላፊው የተናገሩት።
ምንም አይነት የመታወቂያ ወረቀት የሌላቸው ሰዎች በጊዜያዊነት የመታወቂያ ወረቀት እንዲያገኙ ብቻ እንድሚደረግም ገልጸዋል።
ከተማዋን ከስጋት ነፃ ለማድረግ የፀጥታ ሀይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በሰራው ስራም በርካታ የጦር መሳሪያዎች፣ ሀሰተኛ የመታወቂያ ወረቀቶች፣ የአገር መከላከያ እና የትግራይ ልዩ ሀይል የደንብ ልብሶችና የተለያዩ የውጭ አገራት ገንዘቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድተዋል።
ህብረተሰቡ አሁንም ከፀጥታ ሀይሉ ጋር በመሆን አካባቢውን እንዲጠብቅም አሳስበዋል።
የምዕራባውያን ጫና ተጠናክሮ ለመቀጠሉ ማሳያ የሆኑ የሽብር መረጃዎችን ወደጎን መተው ይገባል ያሉት ሃላፊው፥ አዲስ አበባ ላይ የተጋረጠ ምንም አይነት የፀጥታ ስጋት የለም ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!