ሰኔ 23/2014 ዓ.ም “እኔም ለከተማዬ ፅዳትና ውበት ባለቤት ነኝ!” በሚል መሪቃል በብሎክ እና በትምህርት ቤቶች ደግሞ ” ትምህርት ቤቴን አፀዳለሁ ፅዱና ውብ በሆነ ከተማ እኖራለሁ!” በሚል መሪቃል አባለፉት 3 ተከታታይ ወራት መጠነ ሰፊ ሁሉን አቀፍ የፅዳት ንቅናቄ ማጠቃለያ መርሃግብሩን በወዳጅነት ፓርክ አከናውኗል::
በማጠቃለያ መርሃግብሩ ላይም የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ መለሰ አለምን ጨምሮ የካቢኔ አባላት : የከተማና የክ/ከተማ አመራሮች : ታዋቂ አርቲስቶች : የሃይማኖት ተቋማት : ባለድርሻ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል::
በተደረገው የፅዳት ንቅናቄ ለዕቅዱ መሳካት የተሻለ አፈፃፀም ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች የእውቅና ምስክር ወረቀት : ዋንጫና ምስጋና ተበርክቶላቸዋል::
በዕለቱም ከወዳደቀ ደረቅ ቆሻሻ በመሰብሰብ መልሶ በመጠቀምና ኡደት በማድረግ የተሰሩ የተለያዩ ጌጣጌጦችን ኤግዚቢሽንና ባዛር ለታዳሚው ለዕይታ ቀርቧል::