እንደሚታወቀው በወለጋ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ተከትሎ በዚህ ሰሞን ከአካባቢው ተፈናቅለው የመጡ ዜጎች ወደ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል፡፡
የከተማ አሰተዳደሩ እነኚህ ዜጎች ወደከተማይቱ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ጊዜያዊ ድጋፎችንና ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ከሚመለከታቸው አካላት ሲሰራና ሲወያይ ቆይቷል፡፡
ይህን መሰረት አድረጎ ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው እስኪመለሱ ድረስ በጊዜያዊነት ሊቆዩበት ስለሚቸለው ቦታ የከተማ አስተዳደሩ ከእነዚሁ ዜጎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
ይህንን ተከትሎም በተፈናቀሉት ዜጎች ፍቃድ ላይ ተመስርቶ በኦሮምያ ክልላዊ መንግስትና በብሄራዊ አደጋ መከላከልና ስራ አመራር ኮሚሽን በጋራ ተፈናቃዮቹ በጊዜያዊነት ሊያርፉበት የሚችል ቦታ እየተመቻቸ ይገኛል፡፡
ይህንን አስመልክቶ ከእውነት የራቁ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላት ስላሉ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ አይነት መረጃዎች ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰብን እንዲህ አይነት መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላትን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በህግ ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል!!